image
image
image
image
image

በልደታ ክፍለ ከተማ የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ ያለመ የትምህርት ጉባኤ ተካሄደ

የካቲት 1, 2018
​የልደታ ክፍለ ከተማ ትምህርት ጽሕፈት ቤት የመጀመሪያው ግማሽ ዓመት የትምህርት ጉባኤውን በድምቀት አካሂዷል። በጉባኤው ላይ የባለፉት ስድስት ወራት የሥራ አፈጻጸም የተገመገመ ሲሆን፣ በቀሪ ወራት ሊከናወኑ በሚገባቸው ዕቅዶች ላይም ሰፊ ውይይት ተደርጓል። በመድረኩ ላይ የተገኙት የክፍለ ከተማው ትምህርት ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ወይዘሮ በላይነሽ ሞሲሳ እንደገለጹት፤ ጉባኤው በትምህርት ስራዎች ላይ ጠንካራ አፈጻጸም ያሳዩ ተቋማትን እውቅና በመስጠት ለቀጣይ ስራ የሚያበረታታ መሆኑን ጠቁመዋል። ወ/ሮ በላይነሽ አክለዉም "ይህ መድረክ ልምድ ምንለዋወጥበትና በከተማ ደረጃ ያለንን የትምህርት ጥራት ተወዳዳሪነታችንን ለማሻሻል ትልቅ ፋይዳ አለዉ ብለዋል። በዕለቱም በመጀመሪያው መንፈቅ ዓመት በትምህርት ስራዎች ላይ የላቀ አፈጻጸም ላሳዩ የትምህርት ተቋማትና ባለድርሻ አካላት የዕውቅና እና የሽልማት መርሃ-ግብር ተካሂዷል።

መልዕክትዎን ይላኩ

ሌሎች ዜናዎች