image
image
image
image
image

የልደታ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ጽ/ቤት የ2018 ዓ.ም 11ኛው ክፍለ ከተማ አቀፍ የተማሪዎች ስፖርት ሊግና የመምህራን ስፖርታዊ ውድድር መክፈቻ ፕሮግራም አካሄደ።

ጥር 1, 2018
ስፓርታዊ ውድድሩ በአካሉ ብቁና በአዕምሮው ንቁ ትውልድ ለሀገር ብልጽግና በሚል መሪ ቃል እየተከናወነ ሲሆን ተማሪዎች ያላቸውን ክህሎት ለማሳደግ የሚያስችል መሆኑ በፕሮግራሙ ላይ ተገልጿል። በፕሮግራሙ ላይ የተገኙት የትምህርት ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ በላይነሽ ሞሲሳ እንዳሉት ትምህርት ቤቶች ተተኪ ስፖርተኞችን በማፍራት ያላቸው ሚና ትልቅ መሆኑን በማንሳት ውድድሩ ይህን ዓላማ ያሳካ እንዲሆን በውድድሩ ላይ የሚሳተፉ ተማሪዎችና መምህራን እንዲሁም ደጋፊዎች ስፖርታዊ ጨዋነትን በመላበስ ውድድሮችን ሊካሄዱ እንደሚገባቸው መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል። ውድድሩ ከጥር 1-15 የሚካሄድ ሲሆን የትምህርት ቤት ማህበረሰቦች በስታዲየም በመገኘት ስፖርተኞችን እንዲያበረታቱ ጥሪ ቀርቧል።

መልዕክትዎን ይላኩ

ሌሎች ዜናዎች