image
image
image
image
image

የልደታ ክ/ከተማ አስተዳደር ትምህርት ጽ/ቤት የማህበራዊ ልማት ክላስተር አደረጃጀት ከሚመለከታቸው የጽ/ቤት ኃላፊዎች ጋር በ2ኛ ሩብ ዓመት በቅንጅት የተሠሩ ስራዎችን ገመገመ።

ጥር 10, 2017
ማህበራዊ ልማት ክላስተር አደረጃጀት በ 2018 ዓ.ም 2ኛ ሩብ ዓመት በአዲስ መልክ የተደራጀ ሲሆን በተለይ አደረጃጀቱ ከተዋቀረ በኋላ በትስስር የተከናወኑ ተግባራት በዝርዝር ቀርበው ውይይት ተደርጓል። የትምህርት ጽ/ቤት ኃላፊ እና የክላስተሩ አስተባባሪ የሆኑት ወ/ሮ በላይነሽ ሞሲሳ ውይይቱን የመሩ ሲሆን ክላስተሩ ከተቋቋመበት ጊዜ ጀምሮ በታቀደው ዕቅድ መሠረት በርካታ ስራዎች መሠራታቸውን ገልጸው በተደረገው ትስስር ዜጎች በተለያየ መልኩ ተጠቃሚ መሆናቸውን እንዲሁም በትግበራ ምዕራፍ የተሰሩ በርካታ ስራዎች አበረታችና ተስፋ ሰጭ መሆናቸውን ገልጸው ይሄንን መልካም ተግባር አጠናክረን መቀጠል ይኖርብናል ሲሉ ተናግረዋል። በማህበራዊ ልማት ክላስተር አደረጃጀት ከትምህርት ጽ/ቤት ጋር ትስስር ያደረጉ የየጽ/ቤቱ ኃላፊዎችም በበኩላቸው በቅንጅት የምንሰራውን ስራ ከዚህ የተሻለ አጠናክረን በመቀጠል ሁላችንም የሚጠበቅብንን ኃላፊነት ልንወጣ ይገባል ሲሉ ተናግረዋል። በመጨረሻም በማህበራዊ ልማት ክላስተር አደረጃጀት በቅንጅት ውጤታማ ስራ ለሰሩ ተቋማት የማበረታቻ ሰርተፍኬት ተሰጥቷል።

መልዕክትዎን ይላኩ