image
image
image
image
image

​የልደታ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ጽ/ቤት የ2018 ዓ.ም የመጀመሪያ ግማሽ ዓመት የትምህርት ጉባኤውን በድምቀት አካሄደ።

ጥር 28, 2017
በጉባዔው ላይ በሃገር ደረጃ የተማሪ ወላጅ ማህበር ፕሬዚዳንት አቶ ሃሰን ሺፋን ጨምሮ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች እና ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል። የትምህርት ጽህፈት ቤት ኃላፊ ወ/ሮ በላይነሽ ሞሲሳ በመክፈቻ ንግግራቸው እንደተናገሩት በተለይ በ2018 ዓ.ም የተማሪዎችን ውጤት ለማሻሻል በከተማ ደረጃ አዳዲስ ስትራቴጂዎች ተቀርጸው ተግባራዊ እየተደረገ መሆኑን ገልጸው ይሄንንም ከግብ ለማድረስ ሁላችንም በየደረጃው ቁርጠኛ በመሆን የተማሪዎች ውጤት መሻሻል ላይ ሚናችንን መወጣት ያስፈልጋል ብለዋል። ወ/ሮ በላይነሽ አክለዉም ይህ መድረክ ልምድ ምንለዋወጥበትና በከተማ ደረጃ ያለንን የትምህርት ጥራት ተወዳዳሪነታችንን ለማሻሻል ትልቅ ፋይዳ አለዉ ብለዋል። በጉባኤው ላይ ባለፉት ስድስት ወራት የሥራ አፈጻጸም የተገመገመ ሲሆን በቀሪ ወራት ሊከናወኑ በሚገባቸው ዕቅዶች ላይም ሰፊ ውይይት ተደርጓል። በመጨረሻም በ2018 ዓ.ም የመጀመሪያ መንፈቅ ዓመት በክፍለ ከተማ ደረጃ በተደረገ ምዘና የላቀ አፈጻጸም ላሳዩ የትምህርት ተቋማትና ባለድርሻ አካላት የዕውቅና እና የሽልማት መርሃ-ግብር ተካሂዷል።

መልዕክትዎን ይላኩ