የልደታ ክፍለ ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት በሪፎርምና በለውጥ ስራዎች ላይ ያስመዘገባቸውን ውጤቶችን የተመለከተ የልምድ ልውውጥ ፕሮግራም አካሄደ።

ታህሳስ 11, 2017      Admin
በፕሮግራሙ ላይ የከተማው ትምህርት ቢሮና ሁሉም ክፍለ ከተሞች የተሳተፉ ሲሆን የተገኙት ልምዶች እንዲሰፉ የሚያደርግ መሆኑ ተገልጿል። የአዲስ አበባ ከተማ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ዘላለም ሙላቱ እንደተናገሩት በልደታ ክፍለ ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት በሪፎርምና ለውጥ ስራዎች የተመዘገቡ ውጤቶች በጽ/ቤቱ አመራሮች፣ባለሙያዎችና የትምህርቱ ማህበረሰብ ትብብር የመጣ መሆኑንና በጽ/ቤቱ የተመዘገቡ የሪፎርምና የለውጥ ስራዎች እንዲሁም ሌሎች የጽ/ቤቱን ውጤታማ ስራዎች ወደሁሉም ክፍለ ከተሞች ሊሰፉ ይገባል ብለዋል። የልደታ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ዋና ስራ አስፈጻሚ ወ/ሮ አበባ እሸቴ በበኩላቸው በትምህርት ጽ/ቤት እየተከናወኑ የሚገኙ የለውጥና የሪፎርም ስራዎች ርስ በርስ መማማርን በማሳደግ የተማሪዎች ውጤት እንዲሻሻል የሚያደርጉ መሆናቸውን በመግለጽ በትምህርት ቤት አካባቢ የሚስተዋሉ አዋኪ ድርጊቶችን በማስወገድና ባለድርሻ አካላትን በማሳተፍ እየተሻሻለ የመጣውን መማር ማስተማርና የተማሪዎችን ውጤታማነት ልናስቀጥል ይገባል ብለዋል። የልደታ ክፍለ ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አሰፋ ግርማ እንደገለጹት የተማሪዎች ውጤት እንዲሻሻል ለጽ/ቤቱ ሰራተኞችና ለመምህራን የተለያዩ ስልጠናዎችን በማዘጋጀት በመማር ማስተማሩ ላይ ብቁ እንዲሆኑ እያደረጉ መሆኑን በማንሳት እየተከናወኑ የሚገኙ ጥሩ አፈጻጸሞችን በማስቀጠል የተማሪዎች ውጤት እንዲሻሻል እንሰራለን ብለዋል። የውይይቱ ተሳታፊዎች እንደገለጹት በትምህርት ጽ/ቤት የተሰሩ ስራዎች በተቋሙ ውስጥ ርስ በርስ መማማርን በማጎልበት የተማሪዎች ውጤት እንዲሻሻል የሚያደርጉ በመሆናቸው ወደተቋማችን በማስፋት ለተማሪዎች ውጤት መሻሻል ልንጠቀምባቸው ይገባል ብለዋል።

ተያያዥ መረጃዎች