የልደታ ክ/ከተማ አስተዳደር ትምህርት ጽ/ቤት የሰኞ ማለዳ ከስራ ሰዓት መግቢያ በፊት የሚያዘጋጀው የሰራተኞች የዕውቀት ሽግግር መርሀ ግብር አካሄደ።

መጋቢት 29, 2017      Admin
በመርሃ ግብሩ ላይ የትምህርት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አሠፋ ግርማ፣ የማኔጅመንት አባላትና አጠቃላይ ሰራተኞች ተገኝተዋል። በጽ/ቤቱ የ2ኛ ደረጃ አጠቃላይ ትምህርት ሱፐርቫይዘር የሆኑት አቶ ለይኩን ብርሃኑ "ተቋማዊ ባህልን መገንባት" በሚል ርዕስ እውቀታቸውን ያካፈሉ ሲሆን "ተቋማዊ ባህል ምንድነው?" "ተቋማዊ ባህል በምን ይገለጻል?" "የእኛ ተቋማዊ ባህል ምን ምን ናቸው?" "የተቋማዊ ባህል አይነቶች" እና ሌሎችም ርዕሶችን አካተው እውቀታቸውን አካፍለዋል። የትምህርት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አሠፋ ግርማ በንግግራቸው ትምህርት ጽ/ቤት ላለፉት ተከታታይ ዓመታት ውጤታማ መሆኑ፣ ከፍተኛ የሆነ የስራ ተነሳሽነት መኖር፣ በጋራ ሰርቶ በጋራ ማደግ እና ሌሎችም ሊጠቀሱ የሚችሉ በርካታ ርዕሰ ጉዳዮች የጽ/ቤቱ ጠንካራ ተቋማዊ ባህል መሆኑ እና ሌሎች ከእኛ ሊማሩት የሚገባ ነው ሲሉ ተናግረዋል። አያይዘውም እሴቶቻችን ብለን ያስቀመጥናቸውን ከወረቀት በዘለለ ባህላችን ማድረግ ይኖርብናል ብለዋል። በጽ/ቤቱ የቡድኖች አስተባባሪ የሆኑት አቶ ገዳ ሞሲሳ በበኩላቸው እንደ ልደታ ክ/ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት ተቋማዊ ባህል አድርገን ካዳበርናቸው እና የእኛ መገለጫ ካደረግናቸው ተግባራት መካከል አብሮ መስራት፣ ተጨማሪ ስራዎችን ከፋፍሎ መስጠትና ተግባራዊ ማድረግ፣ ኃላፊ ኖረም አልኖረም ስራዎች መሰራታቸው የጽ/ቤታችን ተቋማዊ ባህላችን ነው ሲሉ ገልጸዋል። የጽ/ቤታችን ባለሙያዎች በበኩላቸው እንደ ጽ/ቤት ጠንካራ ተቋማዊ ባህላችንን አጠናክረን እንቀጥላለን ሲሉ ተናግረዋል።

ተያያዥ መረጃዎች