የልደታ ክ/ከተማ አስተዳደር ትምህርት ጽ/ቤት የሰኞ ማለዳ ከስራ ሰዓት መግቢያ በፊት የሚያዘጋጀው የሰራተኞች የዕውቀት ሽግግር መርሀ ግብር አካሄደ።

ሚያዚያ 28, 2017      Admin
የሰኞ ማለዳ የሰራተኞች የዕውቀት ሽግግር መርሀ ግብር ተካሄደ፡፡ በመርሃ ግብሩ ላይ የትምህርት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አሠፋ ግርማ፣ የማኔጅመንት አባላትና አጠቃላይ ሰራተኞች ተገኝተዋል። በጽ/ቤቱ የመምህራንና የትምህርት አመራር ልማት ባለሙያ የሆኑት አቶ አሸናፊ ተሾመ "የእውቀት ሽግግር ጽንሰ ሃሳብ" ላይ እውቀታቸውን አካፍለዋል። የእውቀት ሽግግር ጽንሰ ሃሳብ/ትርጓሜ፣ የእውቀት ዓይነቶች፣ የእውቀት ሽግግር ጠቀሜታ፣ እውቀት መቼ፣ እንዴት፣ ለማን እና ከማን ይሸጋገራል እንዲሁም የእውቀት ሽግግር ሂደቶች [Identifying... prioritizing... Capturing & Transfering... Sharing & Storing] እና ሌሎች ርዕሶችን አስመልክቶ አቶ አሸናፊ በዝርዝር አስረድተዋል። የትምህርት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አሠፋ ግርማ በንግግራቸው የእለቱ ርዕስ በቀጥታ ከእውቀት ሽግግር ዓላማ ጋር የሚያያዝ ጽንሰ ሃሳቡን ጠንቅቆ ለመረዳት የሚጠቅም መሆኑን ገልጸዋል። በጽ/ቤቱ የቡድኖች አስተባባሪ የሆኑት አቶ ገዳ ሞሲሳ በበኩላቸው በየሳምንቱ የሚቀርቡ ርዕሶች ይበልጥ የሚያነቃቁ መሆኑን እና በጽ/ቤቱ ያለውን እምቅ እውቀት አንዳችን ለአንዳችን እየተካፈልን መገነባባቱን በሚገባ አጠናክረን እንቀጥላለን ብለዋል።

ተያያዥ መረጃዎች