የልደታ ክ/ከተማ አስተዳደር ትምህርት ጽ/ቤት 10ኛው ከተማ አቀፍ የሳይንስና የፈጠራ ስራ አውደ ርዕይ ላይ በአጠቃላይ ድምር ውጤት 2ኛ ደረጃ በመውጣት የዋንጫ እና የሠርተፍኬት ተሸላሚ ሆነ።

ሚያዚያ 18, 2017      Admin
****እንኳን ደስስስስ አለን!!!**** የልደታ ክ/ከተማ አስተዳደር ትምህርት ጽ/ቤት 10ኛው ከተማ አቀፍ የሳይንስና የፈጠራ ስራ አውደ ርዕይ ላይ በአጠቃላይ ድምር ውጤት 2ኛ ደረጃ በመውጣት የዋንጫ እና የሠርተፍኬት ተሸላሚ ሆነ። ባለፉት 3 ተከታታይ ቀናት ሲካሄድ በቆየው የመምህራን እና የተማሪዎች የሳይንስና ፈጠራ ውድድር የልደታ ክ/ከተማ አስተዳደር ትምህርት ጽ/ቤት በአጠቃላይ 11 ሜዳሊያ፣ 11 ሠርተፍኬት እና 1 ዋንጫ በማምጣት ተሸላሚ ሆኗል። የልደታ ክ/ከተማ አስተዳደር ትምህርት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አሠፋ ግርማ በሳይንስና ፈጠራ ስራው ባስመዘገብነው ድል የተሠማቸውን ደስታ የገለጹ ሲሆን ለዚህ ስኬት መመዝገብ የአንበሳውን ድርሻ ለወሰዱ መምህራን እና ተማሪዎች እንዲሁም ከቅድመ ዝግጅት ጀምሮ እስከ ማጠቃለያው ድረስ ለደከሙ የጽ/ቤቱ አስተባባሪዎች፣ ቡድን መሪዎች፣ ሱፐርቫይዘሮችና ባለሙያዎች፣ የወረዳ አመራሮች፣ የት/ቤት ርዕሳነ መምህራን እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ላቅ ያለ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

ተያያዥ መረጃዎች