የልደታ ክ/ከተማ አስተዳደር ትምህርት ጽ/ቤት በተማሪዎች ምገባ ዙሪያ በ3ኛ ሩብ ዓመት የተደረገ ክትትልና ድጋፍ ግኝት ከጽ/ቤቱ ባለሙያዎች ጋር ገመገመ።

ሚያዚያ 6, 2017      Admin
የተደራጁ ማህበራት ህጋዊ ፈቃድ ያላቸው ስለመሆኑ፣ ከት/ቤቱ ጋር ውል ስለመዋዋላቸው እና ውሉ ስለመታደሱ፣ በተመጋቢ ተማሪዎች ቁጥር መሠረት ክፍያ እየተፈጸመ ስለመሆኑ፣ የምግብ ሜኑ ሳይሸራረፍና በተገቢው ሠዓት ተግባራዊ ስለመደረጉ፣ የምግብ ዝግጅት እና የመመገቢያ አዳራሽ ንጽሕና እና ሌሎች በርካታ ጉዳዮች በቼክሊስቱ የተካተቱ ጉዳዮች ናቸው። በጽ/ቤቱ የልዩ ፍላጎት እና ዘርፈ ብዙ ጉዳዮች ቡድን መሪ የሆኑት ወ/ሮ ዘውዱ መሃሪ በእያንዳንዱ ተግባር የት/ቤቶች ጥንካሬ እና የነበሩ ክፍተቶችን ያቀረቡ ሲሆን በተለይ የምግብ ሜኑ በአግባቡ አለመተግበር፣ የውል እድሳት አለማድረግ፣ የምገባ ኮሚቴዎች አስፈላጊውን ድጋፍና ክትትል አለማድረግ፣ የጠራ መረጃ አለመኖር እንዲሁም ብልሹ አሠራሮች መኖራቸው በክፍተት የሚገለጹ ዋና ጉዳዮች መሆኑን ወ/ሮ ዘውዱ አብራርተዋል። በጽ/ቤቱ የቡድኖች አስተባባሪ የሆኑት አቶ አቡበከር አህመድ በበኩላቸው እንደተናገሩት በተማሪዎች ምገባ ዙሪያ በርካታ የተሰሩ ስራዎች ቢኖሩም አሁንም ድረስ ያልተቀረፉ ብልሹ አሠራሮች መኖራቸውን ገልጸው ይሄንንም ለማስተካከል እንደ ጽ/ቤት እርምጃ መወሰዱን እና በቀጣይም አጠናክረን የምንቀጥል መሆኑን ጭምር አጽንዖት ሰጥተው ተናግረዋል።

ተያያዥ መረጃዎች