በዛሬው የእውቀት ሽግግር ባለፉት ዘጠኝ ወራት ውስጥ የተሠሩ ስራዎች የተገመገሙ ሲሆን የእቅድና ሪፖርት ዝግጅት እና አተገባበር፣ የተማሪ ውጤት እና ስነምግባር ማሻሻል፣ የመልካም አስተዳደርና ብልሹ አሠራር፣ አገልግሎት አሠጣጥ፣ የትምህርት ንቅናቄ እንዲሁም የቴክኖሎጂ አጠቃቀም የትኩረት ነጥቦች በማድረግ ውይይት ተካሂዷል።

ሚያዚያ 6, 2017      Admin
በቀረቡት የመወያያ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ 6ቱም የስራ ቡድኖች ያስመዘገቡትን ውጤት እና ያጋጠሙ ችግሮችን አቅርበዋል። የትምህርት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አሠፋ ግርማ በግምገማው ላይ እንደተናገሩት ተቋሙ በእቅድ መመራቱ እና እቅዶች መገምገማቸው፣ የተማሪ ውጤትና ስነምግባር ላይ ለውጥ መምጣቱ፣ ሠላማዊ የመማር ማስተማር ሂደት መኖሩ፣ አገልግሎት አሠጣጥ ላይ በጥንካሬ የሚነሱ በርካታ ተግባራት መኖራቸው፣ የቴክኖሎጂ አጠቃወም እንዲሁም የክትትልና ድጋፍ አግባባችን በጥንካሬ የሚገለጹ መሆኑን ጠቅሰው ሆኖም ግን የምንሰራቸው ተግባራት ምን ያህል ውጤታማ አድርጎናል የሚለውን ግን ቆም ብለን ማየት እና ማስተዋል ይኖርብናል ብለዋል። በጽ/ቤቱ የቡድኖች አስተባባሪ የሆኑት አቶ ገዳ ሞሲሳ በበኩላቸው የተማሪዎችን ውጤት ለማሻሻል እቅድ ከማዘጋጀት ጀምሮ ሞዴል ፈተናዎች መሰጠቱ፣ ጥያቄና መልስ ውድድር መካሄዱ፣ በርካታ ክትትልና ድጋፎች መደረጋቸው፣ ካለፉት አመታት አንጻር የተማሪዎች የቡድን ጸብ የቀነሰ መሆኑ፣ በሪፎርም ስራዎች በከተማ እና በክ/ከተማ ደረጃ ልምድ ማካፈላችን በጥንካሬ የሚገለጹ ሲሆን የመረጃ ጥራት፣ የእቅድና ሪፖርት ጥራት እንዲሁም የተማሪዎች ምገባ ስርዓት ላይ ክፍተት መኖሩን አያይዘው ገልጸዋል። በጽ/ቤቱ የቡድኖች አስተባባሪ የሆኑት አቶ አቡበከር አህመድ በተመሳሳይ ከእቅድ ዝግጅት ጀምሮ እስከ አፈጻጸሙ ድረስ ያሉ ጥንካሬዎችን ገልጸው በተለይ በተቀመጠው የግንኙነት ጊዜ መሠረት ስራዎችን እየገመገሙ መሄድ፣ በተቀመጠው የጊዜ ገደብ መሠረት ወርሃዊ ሪፖርቶች ገቢ አለመሆን እንዲሁም ከተማሪዎች ምገባ ጋር ተያይዞ ክፍተቶች መኖሩን አቶ አቡበከር ገልጸዋል።

ተያያዥ መረጃዎች