የመንግስት መስሪያ ቤቶች የሠው ኃይል ስምሪት በልዩ ሁኔታ ለማመጣጠን የወጣ የዝውውር ምደባ ደንብ ቁጥር 179/2017 አስመልክቶ ለሚመለከታቸው አካላት ትውውቅ ተደረገ።

መጋቢት 15, 2017      Admin
የልደታ ክ/ከተማ አስተዳደር ትምህርት ጽ/ቤት የሠው ኃይል ስምሪት በልዩ ሁኔታ ለማመጣጠን የወጣውን የዝውውር ምደባ ደንብ ቁጥር 179/2017 በዛሬው ዕለት አስተዋውቋል። በትምህርት ጽ/ቤት የአፋን ኦሮሞ ስርዓተ ትምህርት ክትትልና ትግበራ ቡድን መሪ የሆኑት አቶ አበራ ቶሎሳ ሰነዱን አቅርበዋል። የዝውውር ምደባው ከከተማ እስከ ት/ቤቶች (መምህራንን አያካትትም) ያለውን የሰው ሃብት አስተዳደር ባሉ የመንግስት መስሪያ ቤቶች ላይ ተፈፃሚ መሆኑ የተገለጸ ሲሆን ይህ ዝውውር በዋናነት ያስፈለገበት ምክንያት ከፍተኛ የሰው ሀይል ካለበት ወደ ዝቅተኛ የሰው ኃይል ያለባቸውን ተቋማቶች የሰው ሀይሉን በማመጣጠን የአገልግሎት አሰጣጡን በማቀላጠፍ የመልካም አስተደደር ችግሮችን ለመቅረፍ ታሳቢ ያደረገ መሆኑ ተገልጿል። በሰነድ ትውውቁ ላይ ሁሉም የክ/ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት ቡድን መሪዎች እና ባለሙያዎች እንዲሁም የወረዳ ትምህርት ጽ/ቤት ኃላፊዎች፣ ቡድን መሪዎች እና ባለሙያዎች ተገኝተዋል። በቀረበው ሰነድ ላይ ለቀረቡ ጥያቄዎች የጽ/ቤቱ የቡድኖች አስተባባሪ የሆኑት አቶ ገዳ ሞሲሳ እና ሰነዱን ያቀረቡት አቶ አበራ ቶሎሳ ምላሽ ሰጥተዋል።

ተያያዥ መረጃዎች