የልደታ ክ/ከተማ አስተዳደር ትምህርት ጽ/ቤት የሰኞ ማለዳ ከስራ ሰዓት መግቢያ በፊት የሚያዘጋጀው የሰራተኞች የዕውቀት ሽግግር መርሀ ግብር አካሄደ።

ግንቦት 4, 2017      Admin
"A mother is she who can take the place of all others but whose place no one else can take." ~~እንኳን ለእናቶች ቀን አደረሳችሁ!~~ በጽ/ቤቱ የአጠቃላይ ትምህርት ሱፐርቪዥን ክላስተር አስተባባሪ የሆኑት ወ/ሮ አበባ ወረታ በኢትዮጵያ የእናቶች ቀን ታሪክ እና አከባበር ላይ እውቀታቸውን አካፍለዋል። ወ/ሮ አበባ የእናቶች ቀን በኢትዮጵያ በሁለት አይነት መልኩ (ባህላዊ እና ዘመናዊ የእናቶች ቀን) የሚከበር መሆኑን ገልጸው ባህላዊ የእናቶች ቀን በተለይ በደቡብ ኢትዮጵያ ከጥንት ጀምሮ የሚከበር እና ለአንድ ቀን ብቻ ሳይሆን ለተከታታይ ቀናት እናትነትን በሚያወድሱ መዝሙሮች፣ ጭፈራዎች፣ ቤተሰባዊ ታሪኮችን በመለዋወጥ እንዲሁም ባህላዊ ምግቦችን በማዘጋጀት የሚከበር መሆኑን እና ዋናው ዓላማ የቤተሰብን ትስስር ለማጠናከር እና የሴቶችን ማዕከላዊ ሚና ለማጉላት የሚከበር በዓል መሆኑን ገልጸዋል። አያይዘውም ዘመናዊ የእናቶች ቀን በየዓመቱ በግንቦት ወር 2ኛ ሳምንት (እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር) እለተ እሁድ ላይ የሚከበር እንደሆነና በተለይ በከተሞች አካባቢ እውቅና ያገኘ የአከባበር አይነት መሆኑን፣ ለእናቶች ካርዶችን፣ ስጦታዎችን እና አበባ በመስጠት የሚከበርና በእለቱም እናት እረፍት እንድታደርግ በማድረግ በልዩ ሁኔታ እንክብካቤ ማድረግን የሚያካትት መሆኑን ወ/ሮ አበባ ገልጸዋል። በጽ/ቤቱ የቡድኖች አስተባባሪ የሆኑት አቶ ገዳ ሞሲሳ በማጠቃለያ ንግግራቸው እናትነት ጸጋ መሆኑን፣ ክብር መሆኑን እንዲሁም እናትነት ጥልቅ መሆኑን እና እናትነትን በ20 ደቂቃ ብቻ የምንገልጸው ጉዳይ አለመሆኑን ገልጸው ለሁሉም እናቶች የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

ተያያዥ መረጃዎች