የልደታ ክ/ከተማ አስተዳደር ትምህርት ጽ/ቤት ለ6ኛ፣ ለ8ኛ እና ለ12ኛ ክፍል ተማሪዎች በክ/ከተማ ደረጃ ለሚሰጠው የሞዴል ፈተና ዝግጅት በTable of Specification አዘገጃጀት ዙሪያ ፈተናውን ለሚያዘጋጁ መምህራን ግንዛቤ ሰጠ።

ሚያዚያ 2, 2017      Admin
በጽ/ቤቱ የቡድኖች አስተባባሪ የሆኑት አቶ ገዳ ሞሲሳ በንግግራቸው እንዳሉት የትምህርት ጥራትን ለማስጠበቅ እንዲሁም የተማሪዎችን ውጤት ለማሻሻል አንዱ ስትራቴጂ ተማሪዎችን በሞዴል ፈተና ማዘጋጀት መሆኑን ጠቅሰው ወጥ የሆነ እና ደረጃውን የጠበቀ ፈተና ለማዘጋጀት Table of Specification ወሳኝ መሆኑን ገልጸዋል። አቶ ገዳ አያይዘውም በቀሩን ጥቂት ወራት የ6ኛ፣ የ8ኛ እና የ12ኛ ክፍል ተማሪዎችን ለሃገር አቀፍ እና ከተማ አቀፍ ፈተና ለማዘጋጀት በከተማ እና በክ/ከተማ ደረጃ የሞዴል ፈተና የሚሰጥ መሆኑን እና ለመምህራን የተሻለ ግንዛቤ ለመፍጠር ታስቦ የተዘጋጀ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ መሆኑን ገልጸዋል። የመረጃና ቴክኖሎጂ ቡድን መሪ የሆኑት አቶ መንግስቱ ኦሳቦ በበኩላቸው በ2ኛው ወሰነ ትምህርት ለ6ኛ፣ ለ8ኛ እና ለ12ኛ ክፍል ተማሪዎችን በሁለቱም መርሃ ግብር እንደ ክ/ከተማ አንድ ሞዴል ፈተና የሚሰጥ መሆኑን እና ሞዴል ፈተናው የሚሰጠው በዋናነት ተማሪዎችን ብቁ እና ተወዳዳሪ ለማድረግ እንዲሁም ፈተናውን የሚያዘጋጁ መምህራን የTable of Specification ጽንሰ ሃሳብ ተረድተው ደረጃውን የጠበቀ ፈተና እንዲያዘጋጁ ለማድረግ ነው ብለዋል። ለበርካታ አመታት በመምህርነት ያገለገሉት መምህር ዮናስ ንብረት በTable of Specification አዘገጃጀት፣ ጽንሰ ሃሳብ፣ ያለውን ጠቀሜታ እና ሌሎችንም ጉዳዮች አንስተው ግንዛቤ ተፈጥሯል።

ተያያዥ መረጃዎች