በመቅደላ ቅድመ 1ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የተገነባው እና ከመጋቢት 24 ፍሬዎች መካከል አንዱ የሆነው ባለ 4 ወለል የመማሪያ ህንጻ ተመርቆ አገልግሎት መስጠት ጀመረ።

መጋቢት 23, 2017      Admin
በመማሪያ ህንጻው የአገልግሎት ማስጀመሪያ መርሀ ግብር የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ አማካሪ አቶ ጥላሁን ፍቃዱ፣የልደታ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አ ፈጻሚ ወይዘሮ አበባ እሸቴ እንዲሁም የክፍለ ከተማው ብልጽግና ፖርቲ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ሀፍቱ ብርሀኑ እና የትምህርት ጽህፈት ቤት ኃላፊው አቶ አሰፋ ግርማን ጨምሮ የክፍለ ከተማውና የወረዳ 6 አመራሮች፣ የትምህርት ቤቱ ርዕሳነ መምህራን ተማሪዎች፣ መምህራን እና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ አማካሪ እና የፕሮግራሙ የክብር እንግዳ አቶ ጥላሁን ፍቃዱ በመርሀ ግብሩ መክፈቻ ባስተላለፉት መልዕክት በመቅደላ ቅድመ አንደኛ እና 1ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በአጭር ጊዜ ጥራቱን ጠብቆ ለአገልግሎት የበቃው ባለ 4 ወለል ህንጻ የኢትዮጵያ ትንሳኤ በተረጋገጠበትና ፕሮጀክቶችን መጀመር ብቻ ሳይሆን መጨረስ እንደሚቻል በተረጋገጠበት መጋቢት 24 ዋዜማ ላይ መሆኑ ለየት እንደሚያደርገው ጠቁመው የመማሪያ ህንጻው በትምህርት ቤቱ ያለውን የተማሪ ክፍል ጥምርታ በማሻሻል የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ እየተከናወኑ የሚገኙ ተግባራትን ውጤታማ የሚያደርግ ተግባር መሆኑን አስገንዝበዋል። የልደታ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አ ፈጻሚ ወይዘሮ አበባ እሸቴ በበኩላቸው በሀገራችን ኢትዮጵያም ሆነ በከተማችን ባለፉት ሰባት አመታት በርካታ ፕሮጀክቶች ተገንብተው ለህብረተሰቡ አገልግሎት በመስጠት ላይ መሆናቸውን ገልጸው በዛሬው እለት ከመጋቢት 24 ፍሬዎች መካከል አንዱ ሆኖ ጥራቱን ጠብቆ በፍጥነት የተገነባው የመማሪያ ህንጻ ለመማር ማስተማር ስራው ውጤታማነት የሚያበረክተው አስተዋጽኦ ከፍተኛ መሆኑን አመላክተዋል። በተመሳሳይ አመራሮቹ በክፍለ ከተማው ከሚገኙ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች መካከል አንዱ በሆነው ከፍተኛ 23 ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ቅጥር ግቢ ውስጥ የሚገነባውን የማስፋፊያ ሁለ ገብ ህንጻ ግንባታ አስጀምረአስጀምረዋል።

ተያያዥ መረጃዎች