የሰኞ ማለዳ የሰራተኞች የዕውቀት ሽግግር መርሀ ግብር ተካሄደ፡፡

መጋቢት 22, 2017      Admin
የልደታ ክ/ከተማ አስተዳደር ትምህርት ጽ/ቤት የሰኞ ማለዳ ከስራ ሰዓት መግቢያ በፊት የሚያዘጋጀው የሰራተኞች የዕውቀት ሽግግር መርሀ ግብር ተካሄደ። በመርሃ ግብሩ ላይ የትምህርት ጽ/ቤት የማኔጅመንት አባላትና አጠቃላይ ሰራተኞች ተገኝተዋል። በልደታ ክ/ከተማ ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሃብት ልማት ጽ/ቤት ባለሙያ የሆኑት አቶ ማርቆስ ለትምህርት ጽ/ቤት ያዘጋጁትን ድረ-ገጽ አስመልክቶ እንዴት መጠቀም እንዳለብን፣ በድረ-ገጹ ላይ ምን ምን ርዕሰ ጉዳዮች እንደተካተቱ አጠቃላይ ገለጻ በማድረግ እውቀታቸውን አካፍለዋል። የትምህርት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አሠፋ ግርማ በንግግራቸው እንዳሉት ከፌስቡክ እና ከቴሌግራም በተጨማሪ ስራዎቻችንን በድረ-ገጽ ማስተዋወቅ እና ማዘመን ይኖርብናል ብለዋል። አያይዘውም የምንሰራቸውን ስራዎች ከፎቶግራፍ በተጨማሪ በቪዲዮ ጭምር መረጃዎችን በመያዝ ለህብረተሰቡ ተደራሽ ማድረግ እና ማስተዋወቅ ይኖርብናል ብለዋል። በጽ/ቤቱ የቡድኖች አስተባባሪ የሆኑት አቶ ገዳ ሞሲሳ በበኩላቸው ድረ-ገጹን ስንጠቀም ጥንቃቄ በተሞላበት መልኩ መሆን እንዳለበት ገልጸው ይሄንን ቴክኖሎጂ በመጠቀማችን እንደ ጽ/ቤት አንድ እርምጃ ወደፊት ቀድመናል ብለዋል። አያይዘውም በተለይ ከቴክኖሎጂ አጠቃቀም ጋር ተያይዞ በጽ/ቤታችን ያሉ የIT ባለሙያዎች እገዛ ማድረግ ይኖርባቸዋል ብለዋል። www.lidetaeducation.gov.et የልደታ ክ/ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት ድረ-ገጽ ነው።

ተያያዥ መረጃዎች