የልደታ ክ/ከተማ አስተዳደር ትምህርት ጽ/ቤት በ6ኛ፣ በ8ኛ እና በ12ኛ ክፍል ተማሪዎች በ10ሩ ወረዳዎች እና በ11ዱ 2ኛ ደረጃ ት/ቤቶች መካከል በሁለቱም መርሃ ግብር የአሸናፊዎች አሸናፊ የጥያቄና መልስ ውድድር አካሄደ።

ሚያዚያ 20, 2017      Admin
የትምህርት ጽ/ቤት የቡድኖች አስተባባሪ የሆኑት አቶ ገዳ ሞሲሳ በመክፈቻ ንግግራቸው በክ/ከተማ ደረጃ የተማሪዎች ውጤት እና ስነምግባር ለማሻሻል የተለያዩ ስትራቴጂዎች እና እቅዶችን በማዘጋጀት በተለይ የሂሳብ እና እንግሊዘኛ ት/ቶች ላይ ልዩ ትኩረት በመስጠት ሲሰራ መቆየቱን ገልጸው ይሄን የጥያቄና መልስ ውድድር ስናዘጋጅ በተማሪዎች እና በተቋማት መካከል ጤናማ የውድድር መንፈስ እንዲፈጠር ለማድረግና በቀጣይ ለሚሰጠው የ6ኛ፣ የ8ኛ እና የ12ኛ ክፍል ክልላዊ እና ሀገር አቀፍ ፈተና ተማሪዎች ራሳቸውን እንዲያዘጋጁ ለማነሳሳትም ጭምር ነው ብለዋል። አቶ ገዳ አያይዘውም ተማሪዎች በቀጣይ በሒሳብ እና እንግሊዝኛ ትምህርቶች ላይ ትኩረት ያደረገ ዝግጅት እንዲያደርጉ ተማሪዎች እና የትምህርት ተቋማት ከወዲሁ መዘጋጀት እንዳለባቸው አሳስበዋል። በት/ቤት እና በወረዳ ደረጃ አሸንፈው የአሸናፊዎች አሸናፊ በመሆን በክ/ከተማ ደረጃ ለውድድር የቀረቡ ተማሪዎች ከመወዳደር ባለፈ የተሻለ አቅም ያላቸውን ተማሪዎች እንዲሳተፉ ማድረግ አዎንታዊ የውድድር መንፈስ ለመፍጠር ጭምር ነው ብለዋል። በውድድሩ ላይ ከ10ሩም ወረዳዎች: 6ኛ ክፍል በአማርኛው ስርዓተ ትምህርት 1ኛ. ተማሪ ኤፍራታ ጌቱ ከወረዳ 2 2ኛ. ተማሪ ያቤጽ ስንታየሁ ከወረዳ 6 3ኛ. ተማሪ ኤልዳና ዮሃንስ ከወረዳ 9 6ኛ ክፍል በአ/ኦሮሞ ስረዓተ ትምህርት 1ኛ. ተማሪ ብሩክ ግርማ ከወረዳ 8 2ኛ. ተማሪ ኢናያ ያፌዝ ከወረዳ 5 3ኛ. ተማሪ ቶሌራ ሰጠኝ ከወረዳ 6 8ኛ ክፍል በአማርኛው ስርዓተ ትምህርት 1ኛ. ተማሪ ማራማዊት እሸቱ ከወረዳ 9 2ኛ. ተማሪ ፌኔት ባህሩ ከወረዳ 6 3ኛ. ተማሪ ሂላል ሻሚል ከወረዳ 2 8ኛ ክፍል በአ/ኦሮሞ ስርዓተ ትምህርት 1ኛ. ተማሪ መባጽዮን ኃይሌ ከወረዳ 6 2ኛ. ተማሪ ባቲሬ አዱኛ ከወረዳ 1 3ኛ. ተማሪ ናፍትሊ አዳነ ከወረዳ 8 በጥቅል በአማርኛ እና በአፋን ኦሮሞ መርሃ ግብር በአንደኛ ደረጃ ከ10ሩ ወረዳ ያሸነፈው ወረዳ። 1ኛ. ወረዳ 6 ትምህርት ጽ/ቤት 2ኛ. ወረዳ 8 ትምህርት ጽ/ቤት 3ኛ. ወረዳ 9 ትምህርት ጽ/ቤት 12ኛ ክፍል በተፈጥሮ ሳይንስ 1ኛ. ተማሪ ብሩክ ሲሳይ ከኔፕስ ት/ቤት 2ኛ. ተማሪ ብሩክ ዘውዱ ከክሩዝ ት/ቤት 3ኛ. ተማሪ መሀመድ ወርቂቾ ከእ/ለፍሬ ት/ቤት 12ኛ ክፍል ማህበራዊ ሳይንስ 1ኛ. ተማሪ ካናን ጎሳዬ ከኦሜጋ ት/ቤት 2ኛ. ተማሪ ያብስራ ደረጄ ከእ/ለፍሬ ት/ቤት 3ኛ. ተማሪ ሰብሪን ዑመር ከኔፕስ ት/ቤት በጥቅል ድምር ውጤት ከ11ዱ 2ኛ ደረጃ ት/ቤቶች:_ 1ኛ. ኔፕስ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት 2ኛ. እውቀት ለፍሬ 2ኛ ደረጃ 3ኛ. ኦሜጋ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት በመጨረሻም በውድድሩ ላሸነፉ ተማሪዎች፣ የወረዳ ት/ጽ/ቤቶች፣ 2ኛ ደረጃ ት/ቤቶች እንዲሁም ጥያቄ ላዘጋጁ መምህራን የተሳትፎ የምስክር ወረቀት፣ አጋዥ መጽሐፍት እና የዋንጫ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።

ተያያዥ መረጃዎች