የልደታ ክ/ከተማ አስተዳደር ትምህርት ጽ/ቤት የ2017 በጀት ዓመት የዘጠኝ ወራት የእቅድ አፈጻጸም ሪፖርት እና በተማሪዎች ምገባ ዙሪያ የተደረገ ክትትልና ድጋፍ ግኝት ባለድርሻ አካላት በተገኙበት ገመገመ።

ሚያዚያ 24, 2017      Admin
በጽ/ቤቱ የቡድኖች አስተባባሪ የሆኑት አቶ አቡበከር አህመድ የዘጠኝ ወራት የእቅድ አፈጻጸም ሪፖርቱን ከግቦች አንጻር የተከናወኑ ተግባራትን አቅርበዋል። በተጨማሪም የሂሳብ እና እንግሊዝኛ ት/ት ለማሻሻል ስትራቴጂው ከወረደበት ጊዜ አንስቶ የተከናወኑ ተግባራትን እንዲሁም ባለፉት ዘጠኝ ወራት ያጋጠሙ ችግሮች እና የተወሰዱ መፍትሄዎችን አቅርበዋል። ከግቦች ጎን ለጎን ሌሎች የተከናወኑ በርካታ ተግባራትንም አቶ አቡበከር አያይዘው አቅርበዋል። በጽ/ቤቱ የልዩ ፍላጎት እና ዘርፈ ብዙ ጉዳዮች ቡድን መሪ የሆኑት ወ/ሮ ዘውዱ መሃሪ በተማሪዎች ምገባ ዙሪያ በ3ኛ ሩብ ዓመት የተደረገ ክትትልና ድጋፍ ግኝት ያቀረቡ ሲሆን በእያንዳንዱ ተግባር የት/ቤቶች ጥንካሬ እና የነበሩ ክፍተቶችን በተለይ የምግብ ሜኑ በአግባቡ አለመተግበር፣ የውል እድሳት አለማድረግ፣ የምገባ ኮሚቴዎች አስፈላጊውን ድጋፍና ክትትል አለማድረግ፣ የጠራ መረጃ አለመኖር እንዲሁም ከምገባ ጋር የተያያዙ ብልሹ አሠራሮች መኖራቸው በክፍተት የሚገለጹ ዋና ጉዳዮች መሆኑን አብራርተዋል። የተደራጁ ማህበራት ህጋዊ ፈቃድ ያላቸው ስለመሆኑ፣ ከት/ቤቱ ጋር ውል ስለመዋዋላቸው እና ውሉ ስለመታደሱ፣ በተመጋቢ ተማሪዎች ቁጥር መሠረት ክፍያ እየተፈጸመ ስለመሆኑ፣ የምግብ ሜኑ ሳይሸራረፍና በተገቢው ሠዓት ተግባራዊ ስለመደረጉ፣ የምግብ ዝግጅት እና የመመገቢያ አዳራሽ ንጽሕና እና ሌሎች በርካታ ጉዳዮች በቼክሊስቱ የተካተቱ ጉዳዮች ናቸው።

ተያያዥ መረጃዎች